ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም
የመንግስተት ዩኒቨርስቲዎች ጋር
በ2017 ዓ/ም በሚተገበሩ ቁልፍ አፈጻጸሞች
ዙሪያ ከሁሉም የዩንቨርሲቲ
ፕሬዝዳንቶች ጋር የስራ ውል መፈራረሙ ይታወቃል። ስራዎችን
ቆጥሮ የመረካከብ እና
ለተረከቡት የስራ ድርሻ
ደግሞ በየደረጃው ካሉ
ሃላፊዎች ጋር ኮንትራት የመፈራረም ሂደት
ዛሬ በድሬደዋ
ዩንቨርሲቲ ተጀምሯል። በዚህ
መሰረት ዛሬ ሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንቶች፣
በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ዳይሬክተሮች እና
የስራ አስፈጻሚ አካላት
ከዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ጋር
የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመዋል።
በፊርማ ስራዓቱ ላይ
የተገኙት የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት
‘’ከዚህ
በኃላ ስራዎችን ቆጥሮ
ተረክቦ በተመሳሳይ ቆጥሮ
የማስረከብ ሂድት እንደሚኖር
አውስተው ከተቀመጠው ቁልፍ
አፈጻጸም መለኪያ በታች
የሚሰሩ የስራ ክፍሎች
ተጠያቂም ጭምር እንደሚሆኑ
ገልጸዋል። እቅዶች እና
ሪፖርቶች በከፍተኛ እና
መካከለኛ አመራሩ ዘንድ
ብቻ ተወስነው
የመቅረት ዝንባሌ መኖሩን
ጠቅሰው ስራዎችን በበለጠ
ሃላፊነት እና ተጠያቂነት ለመከወን ከዝቅተኛ
አመራር አካላት ጀምሮ
እያንዳንዱን የዩንቨርሲቲውን ሰራተኛ
ድርሻ መውሰድ እንደሚገባው
ተናግረዋል።
ዛሬ የተጀመረው
የፊርማ ስርዓት በቀጣይነት
ምክትል ፕሬዝዳንቶች በስራቸው
ከሚገኙ ዳይሬክተሮች፣ ኦፊሰሮች፣
አስተባባሪዎች እና የትምህርት ክፍል ሃላፊዎች
ጋር የፕሬዝዳንት
ጽ/ቤት
ባስቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት እንደሚፈራረሙ
ተጠቁሟል። ዩንቨርሲቲው ከትምህርት
ሚኒስቴር ጋር የተፈራረመውን ኮንትራት ሁሉም
የስራ ክፍሎች ቆርሰው
መውሰዳቸውን እና መተግበሩን የሚያረጋግጥ እንዲሁም
የክትትል እና ድጋፍ ስራን የሚሰራ
ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ
ስራ እንደሚገባም
በመድረኩ ተጠቁሟል።
Share This News