የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።
የስምምነት ሰነዱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ትብብርን በማጠናከር የጥናትና ምርምር ስራን ለማሳደግ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስኮች ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት እና ቴክኖሎጂውን በጋራ ለማልማት ያለመ ነው።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በኢንስቲትዩቱ እየተሰሩ ስላሉ ስራዎች እና ስለስምምነቱን አስፈላጊነት ገለፃ አድርገዋል። ስምምነቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በትብብር እየተሰራ ያለውን ስራ የበለጠ ለማጠናከር እንደሚያግዝ ዋና ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር) በበኩላቸው ስምምነቱ ከኢንስቲትዩቱ ጋር በአጋርነት እንድንሰራ በማስቻል ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቷ አክለውም የኢንስቲትዩቱ እና የዩንቨርሲቲው የዘርፉ ስራዎች አንድ እርምጃ ወደፊት ከፍ እንዲሉ ስምምነቱ ይረዳል ብለዋል።
Share This News