Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ አመራር እና ሰራተኞች የዳዊት አረጋዊያን መርጃ ድርጅትን ለመደገፍ እና ዶ/ር አቤል መልካሙን ለመዘከር በተዘጋጀው የሩጫ ውድድር ላይ ይሳተፋሉ!!

የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ ማህበረሰብ ተኮር ስራዎችን በስፋት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ጥልቅ ማህበራዊ ፋይዳ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ዩንቨርሲቲው ከከተማው ህዝብ እና አስተዳደር ጎን በመቆም እንደሚደግፍ አረጋግጠዋል።

የዳዊት አረጋዊያን መርጃ ድርጅት ባዘጋጀው የሩጫ ውድድርም እርሳቸውን ጨምሮ በርካታ የዩንቨርሲቲው መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎች እንደሚሳተፉም አረጋግጠዋል።

ውድድድሩ አረጋዊያንን ከመደገፍ ባለፈ በዩንቨርሲቲያችን ህክምና ኮሌጅ በተጋባዥ መምህርነት ጭምር ያገለገለውን የህዝብ ልጅ፣ እውነተኛ አገልጋይ እና ሩሩህ ወንድማችንን / አቤል መልካሙን የሚዘክር በመሆኑ የተለየ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

እናትና አባቴን ለመደገፍ እሮጣለሁ!!

/ አቤል መልካሙን ለመዘከር እኔም አለሁ!!

Share This News

Comment