በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ስር ያሉ ቢሮዎች፣ ም/ፕሬዝዳንቶች፣ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮች እና የስራ አስፈጻሚዎች የ6 ወራት የስራ አፈጻጸማቸውን ክፍተኛ አመራሩን ጨምሮ የዩንቨርሲቲው መማክርት (ካውንስል) በተገኘበት አስገምግመዋል። በግምገማው ላይ 13 ቢሮዎች በ6 ወራት ውስጥ የሰሩትን ስራዎች በቁልፍ ተግባር አመላካች እና ትንተናዊ ይዘት ባለው መልኩ ያቀረቡ ሲሆን የቀረቡትን ሰነዶች ልምድ ባላቸው የዩንቨርሲቲው መምህራን እንዲገመገሙ እና ግብረመልስ እንዲሰጣቸው ተደርጓል።
የዘንድሮው አፈጻጸም ግምገማ ለየት ባለ መልኩ እንዲሆን ታቅዶ መዘጋጀቱን የገለጹት የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ግምገማዎች እንደ ከዚህ በፊቱ በጥቂት ግለሰቦች ተሳትፎ ብቻ ተሸፋፍነው የሚታለፉ ሳይሆን በአዳራሽ ከሚነገረው በተጨማሪ የዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ እና አመራሩ የተሰሩትን ስራዎች መገምገም እንዲችል ተደርጓል ብለዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተደረገው የግምገማ ሂደት የተስተዋሉ መልካም ተሞክሮዎችን እና በቀጣይ ሊሰሩ ስለሚገባቸው አንኳር ተቋማዊ ጉዳዮች ገለጻ ያደረጉት ደግሞ የዩንቨርሲቲው ስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ መ/ር ላመስግን አየለ ናቸው። የግምገማው መሰረታዊ ዓላማ በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎችን የጋራ ማድረግ እና ማስተካከያ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተመካክሮ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው ያሉት መ/ር ላመስግን በቀጣይ ሁሉም አመራር በየዘርፉ እቅዱን እና አፈጻጸም ሪፖርቱን በተዋረድ እያቀረበ የጠራ ተቋማዊ ሪፖርት የሚዘጋጅ ይሆናል በማለት ተናግረዋል።
Share This News