በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የስፖርት ውድድር ላይ ተሳትፎ እያደረገ ያለው የድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ የእግር ኳስ ቡድን የቴክኒካል ዩኒቨርሲቲን በመግጠም 4 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።
በተጨማሪም በገበጣ የደባርቅ ዩንቨርሲቲን፣ በቡብ ጨዋታ የመቅደል አምባ ዩንቨርሲቲን በማሸነፍ ድል የቀናው ሲሆን በሴቶች 49kg በታች የሴቶች የቴኳንዶ ውድድር በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሽንፈትን አስተናግዷል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፓርት ውድድር ነገም ሲቀጥል የድሬደዋ ዩንቨርሲቲ በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት ጨዋታዎችን የሚያደርግ ይሆናል።
መልካም እድል ለቡድናችን እንመኛለን!!
Dire Dawa University is found in the industrial and commercial city of Dire Dawa, which is located at 515 km east of Addis Ababa. It is a young higher education institution, established and started its teaching and learning activities in 2007 academic year.
Copyright © 2021 - 2025 Dire Dawa University. All Rights Reserved.
Share This News