Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምስራቅ ክላስተር የተቋማዊ የምርምር ስነ-ምግባር ስልጠና ተሰጠ፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 16 እስከ 17 2017 / ድረስ ሲሰጥ የነበረው የምስራቅ ክላስተር የተቋማዊ የምርምር ስነ-ምግባር ኮሚቴ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በስልጠናው መድረክ መክፈቻ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት / ሰራዊት ሀንዲሶ (በትምህርት ሚኒስቴር፣ የከ///ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች /መሪ ስራ አስፈጻሚ) ሲሆኑ በንግግራቸውም ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ የምርምር ስራዎችን ጥራትና ለአገራዊ እድገት ያላቸውን አስተዋፆ ለማሳደግ እንዲረዳ ምርምሮችን ጭብጥ ተኮር ምርምርን እንዲከተሉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ ገልፀዋል፡፡ ከነዚህም ተግባራት አንዱ የምርምር ስራዎችን የሚያስተባብሩ አመራሮችንና በጭብጥ ተኮር ምርምርምር አሰራር ላይ ግንዛቤያቸውንና ክህሎታቸውን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ይህን ለማሳካት ምርምሮች በምርምር ስነ-ምግባር ኮሚቴዎች ባግባቡ ታይተው ማላፍ እንዳለባቸው በማስገንዘብ የዛሬውን ስልጠና ሁሉም ሰልጣኝ ወደ ተግባር ለመለወጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናው በተሳካ ሆኔታ እንዲካሄድ ያደረገ ሲሆን የዩንቨርሲቲው የምርምር ህትመት፣ ሥነ-ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክተር /ፕሮፌሰር ይታገሱ ስንታየሁ በስልጠናው መዝጊያ ላይ ንግግር አድርገዋል። ከዚህ በፊት የምርምር ስነ-ምግባር የጤና ነክ ምርምሮች ብቻ አድርጎ የመውሰድ ዝንባሌ መኖሩን የገለጹት / ይታገሱ ዛሬ ግን ሁሉም ፊልድ የምርምር ስነ-ምግባር ሂደት ይመለከተኛል የሚል የባለቤትነት ስሜት መፈጠር መቻሉን በመግለጽ የምርምር ስነምግባር በምንሰራው ምርምር ላይ ትልቅ የጥራት ለውጥ ከማምጣቱም በላይ ከምርምር ስራዎች ጋር ተያይዞ ህብረተሰባችን ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ጉዳቶችን በመቀነስ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

በስልጠናው ላይ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (8 ሰልጣኝ) ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (5 ሰልጣኝ) ቀብሪዳር ዩኒቨርሲቲ (7 ሰልጣኝ) እና ሰላሌ የኒቨርሲሰቲ (5 ሰልጣኝ) አሳትፈዋል፡፡ በዚህ ስልጠና 3 ሴቶችና 22 ወንዶች በጥቅሉ 25 ሰልጣኞች ስልጠናውን ወስደዋል፡፡ በስልጠናው ከትምህርት ሚኒስቴር የተጋበዙ 4 አሰልጣን ባካል እና 3 አሰልጣኞች online በመግባት በጥቅሉ 7 አሰልጣኞች ስልጠናውን ሰተዋል፡፡

Share This News

Comment