Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎችን አስመረቀ

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህር መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች በደማቅ ስነ-ሥርዓት አስመርቋል። በምረቃ ስነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ እና የአለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ከድር ጁሃር ''ተማሪዎች ለዓመታት የለፋችሁበትን የድካማችሁን ውጤት በማየታችሁ እንኳን ደስ አላቹ'' በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ክቡር ከንቲባው በማከልም ለተመራቂ ተማሪዎች ስኬት የቤተሰቦቻቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን በማስታወስ በተለያየ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው ልጆቻቸውን በማስተማር ላስመረቁ ቤተሰቦች ምስጋና አቅርበዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም በበኩላቸው ''ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሟቸውን እውቀት እና ክህሎት ተጠቅመው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ እና በሚሰማሩበት የስራ መስክ በታማኝነት እና ቅንነት ለሀገራችን ልማት እንዲሁም ብልጽግና የበኩላቸውን አሻራ እንዲያስቀምጡ አደራ'' ብለዋል።

በዛሬው የምረቃ ስነ -ስርዓት በመደበኛ፣ በተከታታይ እና ክረምት መርሃ ግብሮች በቅድመ ምረቃ 389 እንዲሁም በድህረ ምረቃ 223 በጠቅላላው 612 ተማሪዎች የተመረቁ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 127 በተለያዩ የህክምና ትምህርቶች የተመረቁ ናቸው።

 

Share This News

Comment