Logo
News Photo

በርካታ ተመራማሪዎችን፣ ፓሊሲ አውጪዎች እና ተቋማትን ያሳተፈው 11ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በስኬት ተጠናቀቀ

11ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በስኬት ተጠናቋል፡፡ በተለያዩ ጭብጦች ዙሪያ የተሰሩ 35 የምርምር ውጤቶች በቀረቡበት በዚህ ኮንፍረንስ በርካታ ተጋባዥ ምሁራን፣ የተቋማት መሪዎች፣ ፓሊሲ አውጪዎች እና ተመራማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ /ፕሬዝዳንት / መገርሳ ቃሲም በኮንፍረንሱ መዝጊያ ላይ ባደረጉት ንግግር ዩኒቨርሲቲዎች ተጨባጭ የማህበረሰብ ችግሮችን ለመፍታት ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ጠቁመው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም ከህዝብ እና መንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት እንዲሁም የአካባቢውን ፀጋዎች ማዕከል አድርጎ ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በኮንፍረንሱ ላይ ተሳትፎ ላደረጉ ቁልፍ ንግግር ተናጋሪዎች፣

ተመራማሪዎች፣ ጽሁፍ ገምጋሚዎች፣ ውይይት አመቻቾች እና መሪዎች፣ በየደረጃው ተሳትፎ ላደረጉ የኮንፍረንሱ አዘጋጅ ኮሚቴዎች / መገርሳ ቃሲም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝዳንት የሆኑት / ተማም አወል በበኩላቸው ዘንድሮ የተካሄደው 11ኛው የምርምር ኮንፍረንስ 35 ጭብጥ ተኮር ምርምሮች የቀረቡበት፣ በቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች ዙሪያ ውይይቶች በሰፊው የተደረገበት እንዲሁም ለፓሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የተለዩበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ / ተማም አክለውም ኮንፍረንሱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ እገዛ ላደረጉ አካላት ሁሉ ምስጋና አቅርበው በዚህ ኮንፍረንስ ለመሳተፍ ከተለያዩ ክፍላተ ሃገራት ለመጡ ተመራማሪዎች እና እንግዶች በሰላም ወደ ቤታቸው ይደርሱ ዘንድ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ዛሬ ፍፃሜውን ያገኘው 11ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ 4 ጭብጦች ዙሪያ 35 ምርምሮች የቀረቡበት ስለመሆኑ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

 

Share This News

Comment