በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የተሰሩ የምርምር ውጤቶች ባለድርሻ አካላት እና የዩኒቨርሲቲው መምህራን በተገኙበት ቀርቧል።
በማጠቃለያ መርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝተው አስተያየት የሰጡት የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ተማም አወል ‘’ ዩኒቨርሲቲው በጀት መድቦ የሚያሰራቸው ምርምሮች የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱ እና ተጨባጭ ሀገራዊ ፋይዳ እንዲኖራቸው ታስቦ እንደሆነ በመግለጽ ይህንኑ የዩኒቨርሲቲውን መልካም ተመኩሮ አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት’’ አስረድተዋል። ዶ/ር ተማም በተጨማሪም ‘’ ምርምሮች ተሰርተው ሼልፍ ላይ የሚውሉ ሳይሆን ተጨባጭ አካባቢያዊ እና ሀገራዊ መፍትሄ ጠቋሚ ብሎም መፍትሄ አምጪ እንዲሆኑ ምርምሮች ጭብጥ ተኮር (thematic)፣ አካታች (multi-disciplinary) እና አሳታፊ (ከጾታ አንጻር) እንዲሆኑ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተካሄደው የምርምር ውጤቶች ግምገማ ሂደት (Validation workshop) በተለያዩ የምርምር ርዕሶች እና ተመራማሪዎች የተሰሩ 25 ምርምሮች ለተሳታፊ የቀረቡ ሲሆን ገንቢ የተሳታፊ እና ገምጋሚ መምህራንን አስተያየቶች ባካታተ መልኩ ምርምሮቹ ተሻሽለው እንደሚቀርቡ ከመድረኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
Share This News