Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በራሱ መምህራን ያበለጸገውን የደብዳቤ እና ማህደር አስተዳደር ስርዓት (system) ወደ ስራ አስገባ

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ኃላ ቀር የደብዳቤ ምልልስ እና እንግልትን ያስቀራል የተባለለትን ዲጂታል የደብዳቤ እና ማህደር አስተዳደር ስርዓት ዛሬ ይፋ በማድረግ ወደ ስራ አስገብቷል። 

በስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲትው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ‘’ የደብዳቤ እና ማህደር አስተዳደር ስርዓቱ ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ስራ ከማጠናከሩም ባሻገር ቀድሞ የነበረውን ኃላቀር የደብዳቤ ምልልስ ሂደት እና የሰራተኛ እንግልት በእጅጉ የሚቀንስ መሆኑን በማስታወስ አዲሱን system ላበለጸጉ መምህራን እና ተመራማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል’’ አመልክተዋል።

ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ በማከልም  ‘’ወቅቱን የሚመጥን ዘመናዊ አሰራርን መከተል የግድ መሆኑን ጠቁመው በየደረጃው ያሉ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ቢሮዎች አዲሱን አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ተቋማዊ አሰራራችንን ማዘመን ይጠበቅብናል’’ ሲሉ አጽናኦት ሰጥተው ተናግረዋል። 

የደብዳቤ እና ማህደር አስተዳደር ስርዓቱን ያበለጸጉት የዩኒቨርሲቲው መምህራን ስለአዲሱ አሰራር አጠር ያለ ማብራሪያ በተለይ ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አካላት እና የቢሮ ጸሃፊዎች የሰጡ ሲሆን በቀጣይ በተለይ ለጸሃፊዎች አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት አዲሱን ስርዓት በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።

Share This News

Comment