የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በትኩረት አቅጣጫ በለየው መሰረት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መለየቱ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ለሚያደርገው ሽግግር የሚያግዙ አራት (4) ጥናቶችን በቂ የትምህርት ዝግጅት እና ልምድ ባላቸው የዩኒቨርሲቲው ምሁራን አማካኝነት እየሰራ ይገኛል። ጥናቶቹ በዋናነት
- የዩኒቨርሲቲውን ጥንካሬ፣ ድክመት፣ አስቻይ ሁኔታዎች እና ፈተናዎች የሚዳሥ (SWOT Analysis)፣
- ስልተ ሽግግር (Exit Strategy)፣
- የአተገባበር ሂደት ስልት
(Implementation Strategy) እና
- የግብዓቶች ልየታ እና ቆጠራ (Resource inventories) ናቸው።
እነዚህ ጥናቶች በአብዛኛው የተጠናቀቁ ሲሆን የጥናቶቹን ውጤት በተመለከተ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እና የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል። በቀጣይም ጥናቶቹ ከዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት የቀረቡትን ገንቢ አስተያየቶች መሰረት በማድረግ እርማት ከተደረገባቸው በኃላ ለትግበራ ዝግጁ እንዲሆኑ አቅጣጫ ተቀምጧል።
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከመንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት የአጭር፣ መካከለኛ እና ረዥም ጊዜ እቅድ አዘጋጅቶ እየሰራ መሆኑንም በመድረኩ ተገልጿል።
Share This News