Logo
News Photo

129ኛው የአድዋ ድል በዓል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከብሮ ዋለ

የመላው ዓለም ህዝብ የነጻነት ቀንዲል፣ የጥቁር ህዝቦች እኩልነት ፋና እና የኢትዮጲያዊያን ዘላለማዊ የኩራት ምንጭ የሆነው የዓድዋ ድል በዓል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተከብሮ ውሏል። የዩኒቨርሲቲው የታሪክ እና ፓለቲካል ሳይንስ ምሁራን ድሉን በሚመለከት ያዘጋጁትን ጥናታዊ ጽሁፍም አቅርበዋል።

በዚሁ ዝግጅት ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝዳንት / ተማም አወል የአድዋ ድል የተገኘው ውድ የሆነው የሰው ልጅ ህይወት ተገብሮበት ከጫፍ እስከ ጫፍ ያሉ ኢትዮፒያዊያን ዋጋ ከፍለው የተጎናጸፉት በዓል መሆኑን ተናግረዋል። / ተማም አወል በመቀጠልም ‘’የዓድዋ ድል በዓልን ስናከብር ሀገራችን ለዘመናት የተፈተነችበትን ድህነት እና ኃላቀርነት ለማሸነፍ ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽ በማድረግ ሊሆን ይገባል’’ ሲሉ ተናግረዋል።

በእለቱ የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ የሆኑት / አብዱልከሪም ተመስገን የዓድዋ ድል በተለያዩ መንግስታት ዘመን በነበሩ የታሪክ መጽሃፍቶች ውስጥ ስለተሰጠው ትኩረት እና ዝብርቅርቅ የታሪክ አረዳድ ዙሪያ ደሰሳ አድርጓል። የአድዋ ድል ለአፍሪካዊያን አንድነት ስላበረከተው እና ወደፊትም ስለሚኖረው በጎ ተጽዕኖ የሚዳስስ ጥናት ያቀረቡት ደግሞ የፖለቲካል ሳይንስ ተመራማሪ የሆኑት / ናኒ ደበሌ ናቸው። በመቀጠልም / ደሳለኝ ዋቅጅራ የአድዋን ድልን አስመልክቶ በኢንጊልዝኛ ቋንቋ ግጥም አቅርበዋል።

ጥናታዊ ጽሁፎቹን መሰረት በማድረግ በእለቱ ከተለያዩ የመንግስት ተቋማጥ እና የህብረተሰብ ክፍሎች የተጋበዙ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት በማድረግ የእለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል።

Share This News

Comment