Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ሴት መምህራንን የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ያደረገ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡

የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ጽ/ቤት ያዘጋጀውና ለአንድ ቀን የቆየው የውይይት መድረክ የተቋሙን መምህራን የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ነው፡፡

በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ  አገልግልት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ሲሆኑ በንግግራቸውም በተቋሙ በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ የሴት መምህራን ተሳትፎ ከወንድ መምህራን ጋር ሲነፃፀር አሁንም ድረስ አነስተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ 

በተጨማሪም ዶ/ር ሰለሞን የዚህ የውይይት መድረክ ዋና ዓላማ  በአሁኑ ሰዓት በዩኒቨርሲቲው  የሴት መምህራን በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎት ያላቸው ተሳትፎ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚቃኝበት፣ ተሳትፏቸውንም ለማሳደግ በጽ/ቤቱ የተሰሩ የለውጥ ስራዎች ማስገንዘብ እና በቀጣይ ሴት መምህራን መሰራት ስላለባቸው ተግባራት ለመወያየት ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ይህንን አናሳ የሆነ የሴት መምህራንን የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳትፎ በቀጣይ ለማሳደግ በርካታ ተግባራት ለማከናወን መታቀዱን የጠቀሱት ዶ/ር ሰለሞን ይህንን ማሳካት እንዲቻል ግን የጉዳዩ ዋና ባለቤት የሆኑት ሴት መምህራን አሰተዋፅኦ ከፍተኛ መሆን ይጠበቅበታል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ መምህራን የሴት መምህራንን የምርምርና የማህበረሰብ ተሳትፎ ለማሳደግ ጠቃሚ ናቸው ያሏቸውን ሃሳብና አስተያየት በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡


Share This News

Comment