የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአ/ም/ፕ /ጽ/ቤት በስሩ ያሉትን የተለያዩ ኮሌጆች እና አካዳሚክ ደይሬክተሮች የየካቲት ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለመገምገም እና የመጋቢት ወር እቅድ ለማጽደቅ የካዉንስል ስብሰባ አካሄዷል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአ/ም/ፕ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በመክፈቻ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በገባዉ KPI ስምምነት መሰረት ሰፊ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለጽ የአ/ም/ፕ ጽ/ቤትም እነዚህን ስራዎችን ቆርሶ ወስዶ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የዛሬዉ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ብለዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ሁሉም ዳይሬክተሮች እና ዲኖች በየዘርፋቸው የተቀመጡትን ቁልፍ የሥራ አፈጻጸም አመልካቾች (KPIs) መሰረት በማድረግ ያዘጋጁትን ዝርዝር ሪፖርት እና የመጋቢት ወር እቅድ አቅርበዋል፡፡ በሪፖርቱ የተገኙትን ስኬቶች፣ መሻሻል የሚሹ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።
ውይይቱን ተከትሎ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ ክፍተቶችን ለመሙላት እና የተቋሙን አጠቃላይ አፈጻጸም ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራዊ መፍትሄዎች ተቀምጠዋል። በተጨማሪም የሚያዚያ ወር እቅድ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን እቅዱን ለማሳካት እያንዳንዱ ክፍል በትጋት መስራት እንዳለበት በመግልጽ ስብሰባዉ ተጠናቋል።
Share This News