የዘንድሮው የሴቶች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ114ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ49 ጊዜ
"ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል ፡፡
ይህንኑ በማስመልከትም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት የተከበረ ሲሆን በዚሁ የፓናል ውይይት መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ግርማ ቤካ ዩኒቨርሲቲው የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚ የሚያሳድጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል፡፡
በተለይም ሴት መምህራንን ወደ አመራርነት አንዲመጡ በማድረግና የሴት ተማሪዎች ውጤታማነት ለማሳደግ የተሠሩት ሥራዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
በፓናል ውይይቱ ላይ የፓለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ካሳሁን ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን የማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር ነፃነት ተከስተ ደግሞ
"ሴቶች የሚገጥማቸውን ጫና ተቋቁመው ስኬታማ መሆን ይችላሉ" በሚል ለፓናሉ ተሳታፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡
Share This News