Logo
News Photo

#ኢፍጣር_በድሬዳዋ_ዩኒቨርሲቲ

የረመዳን ጾም ኢፍጣር ዝግጅት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች እና መላው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የዛሬውን የረመዳን ጾም በጋራ አፍጥረዋል። በዚሁ የኢፍጣር ዝግጅት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም እንደተናገሩት ተማሪዎች የረመዳንን ወር በታላቅ ጾም እና ጸሎት ማሳለፋቸው የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ተማሪዎች ከዚህ ባሻገር ትምህርታቸውን በትኩረት እንዲከታተሉ እንዲሁም ድጋፍ የሚሹ ወገኖቻቸውን ከጎናቸው በመሆን እንዲያበረታቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ለመላው ሙስሊም መምህራን፣ ተማሪዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች መልካም የረመዳን ጾም እንዲሆን በድጋሚ ይመኛል።

 رمضان كريم

Share This News

Comment