Logo
News Photo

ሀገራችን በምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሊኖራት የሚገባውን ሚዛናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ።

"ብሔራዊ ጥቅማችን እና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት" በሚል ርዕስ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢ... የሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የፓናል ውይይት ላይ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም "ሀገራችን ኢትዮጵያ በቀጠናው ሊኖራት የሚገባውን ሚዛናዊ ተጠቃሚነት እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጋላጭነቶችን ከመቀነስ አኳያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሚናቸው የጎላ ነው" ብለዋለ፡፡

ፕሬዝደንት / ኡባህ በመቀጠል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ይህንኑ ሚናቸውን ተገንዝበው በተለይም በጥናትና ምርምር እንዲሁም ቀጠናዊ ትስስርና ተጠቃሚነት አስመልክቶ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝደንት የሆኑት / ተማም አወል በበኩላቸው "ቀጠናችን የጋራ መፍትሄዎችን የሚጠይቁ ብዙ ፈተናዎች እና እድሎች ያሉት አካባቢ በመሆኑ የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ በትብብር መንፈስ ልንሰራ ይገባል" ብለዋል።

በሰላም ሚኒስቴር የብሔራዊ መግባባት ዳይሬክቶሬት የብሔራዊ መግባባት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ገዛኽኝ ጥላሁን "ሀገራች በቀጣናው ሊኖራት የሚገባውን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሀገረ መንግስት ግንባታው ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት ሁሉም ዜጋ በሀገሩ ጉዳይ የጋራ አቋም እንዲይዝ ማድረግ አለብን" ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ቤት መምህርት ህሊና አሸናፊ "ብሔራዊ ጥቅማችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት " እንዲሁም የፖለቲካል ሳይንስ መምህሩ ዋኬና ኦፍኬላ "Ethiopias Role in Regional Integration as a Catalyst for Growth and Stability in the Horn of Africa: " በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

Share This News

Comment