Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር የኢድ አልፈጥር በዓልን ከተማሪዎች ጋር አከበረ።

1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችም በዓሉን ከተማሪዎች ጋር በመሆን ያከበሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አገልግሎት ዲን /ቤት እና የተማሪዎች ህብረት በጋራ በመሆን ተማሪዎች በዓሉን በደስታ ያሳልፉ ዘንድ የተለያዩ መርሃ ግብሮችን አዘጋጅተዋል።

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር በእለቱ የምሳ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ለተማሪዎች የእንኳን አደረሳቹ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ በዓሉን ከተማሪዎች ጋር አሳልፈዋል።

 

Share This News

Comment