Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት አጥጋቢ የሆነ የኦዲት አስተያየት እንዲኖር ላደረጉ ሠራተኞች እውቅና ሰጠ፡፡

የፌደራል ዋና ኦዲት መስሪያ ቤት የመንግስት ተቋማትን የፋይናንስ አስተዳደር በየዓመቱ የሚገመግም ሲሆን የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሦስት ዓመታት አጥጋቢ የኦዲት ግኝት ማግኘት ችሏል። ዩኒቨርሲቲው ይህ ስኬት እንዲመዘገብ የአንበሳውን ድርሻ ለተወጡ የተቋሙ የፋይናንስ ክፍል ሰራተኞች ልዩ የእውቅና መርሃ ግብር አዘጋጅቷል።

በእውቅና ፕርግራሙ ላይ በመገኘት ለሠራተኞቹ የምስክር ወረቀት ያበረከቱት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም ላለፋት ሦስት ተከታታ ዓመታት ዩኒቨርስቲያችን አጥጋቢ የሆነ የኦዲት አስተያየት ማግኘት ችሏል፡፡ ለዚህ ውጤት መገኘት ደግሞ በየደረጃው የሚገኙት የዩኒቨርሲቲው የፋናንስ ሠራተኞች እና አመራሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ጠቁመዋል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ እንዲወጣ የሁሉም ሰራተኛ ሚና የጎላ መሆኑን የጠቆሙት / ኡባህ ተቋሙ የጀመረውን ዘርፈ ብዙ ለውጦች ለማገዝ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ በከፍተኛ ተነሳሽነት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

 

Share This News

Comment