በጅቡቲ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ ታሰቦ የዲዛይን ሥራውን ሙሉ በሙሉ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት መምህራን የተሰራው እና በውስጡ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ት/ ቤቶች ያካተተው ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ በዛሬው እለት በጅቡቲ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተ አቶ ቴዎድሮስ ገደፋየ፣ የማህበረሰብ ተወካዮች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በይፉ ተጀመረ።
በፕሮግራሙ ላይ ክቡር አምባሳደር ብርሀኑ ጸጋዬ የት/ቤቱ መገንባት የማህበረሰቡን የረጀም ጊዜ ጥያቄ የሚመልስ እና በሀገራችን ሥርዓተ-ትምህርቶች የመማር እድል የሚሰጥ መሆኑን በመጥቀስ ዩኒቨርሲቲው በዲዛይን ሥራው ላይ ያበረከተውን አስተዋጽኦ እውቅና በመስጠት በቀጣይ በግንባታ ሥራው የማማከር እና ክትትል ላይም በመሳተፍ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
በዩኒቨርሲው ሙሉ ወጪ የተሰራው የቅድመ- ዲዛይን ጥናት እና የዲዛይን ሥራው ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት የገለፁት የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዮት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተ አቶ ቴዎድሮስ ገደፋየ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ከኢንባሲው ጋር በትብብር እንደሚሰራ እና ግንባታውን ከሚያከናውነው የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ጋር በፕሮጀክቱ ግንባታ ወቅት የማማከርና የክትትል ሥራዎችን የሚያከናውን የባለሙያዎች ቡድን በማዋቀር እንደሚላክ አሳውቀዋል።
Share This News