Logo
News Photo

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ለዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት እና አመራርነት ስልጠና ሰጡ።

የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች Design your Future Now በሚል ርዕስ ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም ዓላማቸውን ማሳካት የሚስችላቸው ስልጠና በኢፌድሪ ህዝብ ተወካዮች /ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የድሬደዋ አስተዳደር ሴቶች፣ ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።

በስልጠናው ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ክብርት / ሁክሚያ መሐመድ እንደተናገሩት ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እና ከራሳቸው አልፈው ለሀገርና ለወገን የሚጠቅሙ ዜጋ መሆን እንዲችሉ ከቀደሙት ስኬታማ ሴት አመራሮች ብዙ ጠቃሚ ልምዶችን መቅሰም አለባቸው ብለዋል፡፡

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድና ቱሪዚም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት / አይሻ ያህያ በበኩላቸው የነገው የሀገሪቱ የሴት አመራሮች ተተኪ የሚሆኑት የዛሬ ተማሪዎች መሆናቸውን በመጥቀስ ለዚህም ተማሪዎቹ ጠንክረው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎቹ መልዕክት ያስተላለፉት በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ ቢፍቱ መሀመድ (/) ራስን በመምራትና በጊዜ አጠቃቀም፤ እንዲሁም ራዕይን በመቅረጽ ችግሮችን በማለፍና ስኬታማ ለመሆን መከተል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የህይወት ተሞክሯቸውን መነሻ በማድረግ ለተማረዎች ግንዛቤ አስጨብጠዋል::

የልምድ ልውውጡን ተካፍለው ሲወጡ ያገኘናቸው አንዳንድ ሴት ተማሪዎች እንደነገሩን ‘’ዛሬ ከታላላቆቻችን የቀሰምነው ልምድ ለቀጣይ ህወታችን ስኬት ስንቅ የቋጠርንብት" ነው ሲሉ አስተያት ሰጥተዋል፡፡

 

Share This News

Comment