Logo
News Photo

በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲሁም በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ አደገኛ ዕፆችና ትንባሆ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ውስብስብ ችግሮች ለመከላከል በቅንጅት መንቀሳቀስ ይገባል ተባለ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መቋሚያ የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት (MCDO) እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር "ጤናማ አዕምሮ ለመማር ማስተማሩ ስኬትና ለጤናማ ማኅበረሰብ መሠረት ነው" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጁት የውይይት መድረክ መጋቢት 29/2017 . በድሬድዋ ከተማ ተካሄደ፡፡

በውይይቱ መድረክ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የድሬዳዋ ቅርጫፍ /ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ፍሰሀ እንዳሉት " በአሁኑ ወቅት አደገኛ ዕፆችና የትንባሆ ተጠቃሚነት እንዲሁም የሱስ ተጋላጭነት በከፍተኛ ፍጥነት እየተንሰራፋ መሆኑን ገልጸው በተለይ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዘንድ ችግሩ በስፋት እንደሚስተዋል ገልጸዋል።

በተጨማሪም አቶ ጌቱ " ይሄ ችግር ተማሪዎችን ለውስብስብ ችግር እያጋለጣቸው ስለሆነ ችግሩን ለመቅረፍ በባለስልጣን መስሪያቤቱ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው "ብለዋል፡፡

በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝዳንት / ተማም አወል በበኩላቸው" አደገኛ ዕፆችና የትንባሆ ተጠቃሚነት ሳቢያ በተማሪዎች ላይ ሊመጣ የሚችለው ውስብስብ የጤና እና ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ችግር የሚታይ በመሆኑ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ቀላል የማይባል አሉተዊ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ጠቁመው ይሄንን ወሳኝ የፀረ ሱስ እና የአደገኛ ዕፅ ተጠቃሚነት መከላከል ስራ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

ለአንድ ቀን በቆየው መድረክ የዩኒቨርሲቲ የሚመለከታቸው የስራ ክፍል አመራሮች እና ተማሪዎች መምህራን የድሬዳዋ ፖሊስ ኮምሽን አባላት እና ከተለያዩ የአሰተዳደሩ ሴክትር ምስሪያቤቶች የመጡ ተሳታፊዎች በውይይቱ ተካፋይ የሆኑ ሲሆን በመድረኩም ላይ ከአዲስ አበባ EFDA የተገኙ ባለሙያዎች አቶ ቶለሳ እና የስራ ባልደረባቸው ስለ ትንባሆ እና የሳይኮትሮፒክ መድሃኒቶችን እንዲሁም አቶ ኤልይስ ካልአዩ የመቋሚያ የማህበረሰብ ልማት ድርጅት ዋና ስራስኬያጅ የሆኑት 'ዩኒቨርስቲን መሰረት ያደረገ የፀረ- ሱስ ማህበረሰባዊ ንቅናቄን (UBAACM) " ዋና አላማ እና ዩኒቨርስቲው ከከተማው ማህበረሰብ ጋር ተባብሮ መስራቱ ያለውን አስፈላጊነት ያተኮረ ፅሁፍ ፥በበይነ መረብ ለውይይት መነሻ የሚሆን ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Share This News

Comment