Logo
News Photo

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ አመራሮች የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን የስራ እንቅስቃሴ ክትትል (supervision) አደረጉ

በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደ እና ልማት ዴስክ ሃላፊ አቶ አብዶ ናስር የተመራ ልኡክ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምልከታ አድርጓል። ቡድኑ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የስራ አመራሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል።

የዩኒቨርሲቲው 9 ወር የስራ እንቅስቃሴ ለግብረ ሀይሉ የቀረበ ሲሆን ተቋሙ የጀመራቸው በርካታ የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተጠቁሟል።

 

Share This News

Comment