የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ለአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል። በዚሁ መሰረት ሆስፒታሉን በበላይነት የሚመራው የስራ አመራር ቦርድ የመጀመሪያውን ስብሰባ አድርጓል።
በስብሰባው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ሰብሳቢ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደተናገሩት ‘’ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሪፈራል ሆስፒታል ለከተማችን ነዋሪዎች የህክምና አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑን ጠቁመው የስራ አመራር ቦርዱ ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ ስራ እንዲጀምር እንዲሁም ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት መስጠት እንዲችል ድጋፍ እንደሚያደርግ’’ አረጋግጠዋል።
የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ሁሴን መሀመድ ሆስፒታሉ እስከ አሁን የሰራቸውን ስራዎች ለቦርዱ አቅርበው ውይይት ተደርጓል። የስራ አመራር ቦርዱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።
Share This News