Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ሂውማን ብሪጅ (Human Bridge) ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ግምታዊ ዋጋቸው ከ60 ሚሊየን በላይ የሆነ በርካታ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎለታል። የተለያዩ መመርመሪያ መሳሪያዎች፣ ዘመናዊ የታካሚ አልጋዎች (በሪሞት ኮንትሮል የሚሰሩ)፣ የማዋለጃ ቁሳቁሶች፣ ዊልቸሮች እና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ሆስፒታሉ በድጋፍ መልክ አግኝቷል።

Share This News

Comment