Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምድረ-ገጽ (Landacape) ግንባታ ፕሮጀክትን አስጀመረ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በልዩ ትኩረት ለመስራት ካቀዳቸው የለውጥ ስራዎች ውስጥ አንዱ የሆነው የዩኒቨርሲቲ ምድረ ገጽ ግንባታ ስራ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ማስዋብ፣ ለስራ ምቹ እና ጽዱ የማድረግ አላማን ያነገበው ይህ ፕሮጀክት በከፍተኛ ትኩረት እና ርብርብ እንደሚሰራ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በፕሮጀክት ማስጀመሪያው ላይ ተገኝተው ተናግረዋል። 

ዶ/ር ኡባህ በማከልም ‘ዩኒቨርሲቲውን መሰረታዊ በሚባል መልኩ የማሻሻል እና ለስራ ምቹ የማድረጉን ስራ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በማስታወስ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም በተለይ የምድረ¬-ገጽ ግንባታ ስራውን በመደገፍ እንዲሁም የግቢውን ገጽታ በመጠበቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።’’ 

ፕሮጀክቱን በታለመለት ጊዜ እና ጥራት ለማጠናቀቅ ሁሉም ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚመሩት አምስት አካባቢዎች (zone) የተከፋፈለ ሲሆን ምክትል ፕሬዝዳንቶቹ ክትትል እና ድጋፍ የሚያደርጉላቸው እና ስራውን በሃላፊነት የሚሰሩ አምስት ጥቃቅን እና አነስተኛ ማህበራትም ተመርጠው ለስራ መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል። 

የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር እየተሰሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችንም ተዟዙሮ የተመለከተ ሲሆን ምልከታዎችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የስራ መመሪያዎችንም ሰጥቷል።

Share This News

Comment