በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤቶች እና ዳይሬክቶሬቶች የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን የዩኒቨርሲቲው ካውንስል በተገኘበት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል። በቀጣይም ትኩረት በሚያሻቸው ተግባራት እና አፈፃፀሞች ዙሪያ ርብርብ በማድረግ ተቋሙ በዓመቱ ያቀደውን ግብ ለማሳካት ሁሉም የስራ ክፍሎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እገዛ ሊያደርግ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የዘጠኝ ወር የስራ አፈፃፀም ሪፓርት ግምገማውን የመሩት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ‘’ሁሉም የዩኒቨርሲቲው የስራ ክፍል የሚጠበቅበትን የስራ ሃላፊነት እና ድርሻ ጠንቅቆ በመረዳትና በሀገር ደረጃ ታቅደው በተዋረድ ለተቋማችን የስራ ክፍሎች የተሰጡ ቁልፍ ተግባራትን ማዕከል አድርጎ በመስራት እንዲሁም የስራ አፈፃፀምን በመገምግም ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ ይወጣ ዘንድ ማገዝ ይገባናል’’ ብለዋል።
የቀረቡትን ሪፖርቶች መሰረት አድርጎ የአፈፃፀም ሪፖርቶቹን የገመገሙ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ግብረ መልስ የሰጡ ሲሆን የካውንስል አባላትም ጥያቄዎችን እና ገንቢ አስተያየቶችን ሪፖርቶቻቸውን ላቀረቡ ጽ/ቤቶች ሰጥተዋል። በቀጣይም የተሰጡትን አስተያየት መሰረት በማድረግ ሪፖርቶቹ ማሻሻያ ተደርጎባቸው ለሚመለከተው አካል እንደሚቀርቡ ለማወቅ ተችሏል።
Share This News