Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለስፖርት ሳይንስ መምህራንና ተማሪዎች ፀረ አበረታች መድሃኒትን (ዶፒንግ) አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን  በስልጠና ላይ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና ከድሬደዋ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስፖርት ሳይንስ መምህራን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የሦስተኛ ዓመት ተማሪዎች ተካፋይ ሆነዋል፡፡  

ይህንን ስልጠና በንግግር  የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደተናገሩት ማንኛውም ስፖርተኛ ባልተገባ መንገድ ከሚገኘው ዉጤት ይልቅ ተፈጥሮ በሰጠው በራሱ ጥረትና ድካም የሚገኝ ውጤት አስደሳች እንደሆነና ዘላቂ ደስታን የሚፈጥር መሆኑን ጠቅሰው ስፖርተኞችም ሆነ የስፖርት ባለሙያዎች ስህተቶች እንዳይፈጠሩ አውቀውና ተገንዝበው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።  

በዩኒቨርሲቲው የስፖርት ሳይንስ ት/ት ክፍል ኃላፊ የሆኑት መ/ር ማንደፍሮ ዳኛው በበኩላቸው ት/ት ክፍሉ በፀረ-አበረታች መድኃኒት በኩል ማህበረሰቡን የማስገንዘብ ስራዎችን ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ጋር በጋራ ተቀራርቦ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በስፖርቱ መስክ በዓለም አቀፍ መድረኮች የሃገራችን ስም ማስጠራት የሚችሉ ስፖርተኞችን ለማፍራት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡  

የዚህ አይነት የስልጠና መድረኮች መዘጋጀታቸው ስፖርተኞች ከአበረታች መድሐኒት በፀዳ በራሳቸው አቅምና ችሎታ ብቻ ውድድሮችን እንዲያደርጉ የሚያግዝ ነው ያሉት መ/ር ማንደፍሮ በተለይ ለተመራቂ ተማሪዎቻችን መሰል ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው የተሻለ ግንዛቤን የሚፈጥሩበት መድረክ በመሆኑ ማህበረሰቡን በማስተማር በኩል የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ለአንድ ቀን በቆየው ስልጠና ላይ ከድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና ከድሬደዋ ከተማ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የስፖርት ሳይንስ መምህራን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው የሦስተኛ ዓመት ተማሪዎች ተካፋይ የሆኑበት ሲሆን ሰልታኞቹ ያገኙትን እውቀት ለሌሎች በማካፈል የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡


Share This News

Comment