የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የመንግስት እና የልማት ድርጅቶች ጋር ተቀራርቦ በመስራት ተቋማዊ እና ማህበራዊ ፋይዳቸው የጎላ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው የትብብር ስራዎችን ይበልጥ በሚያጎለብት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የመግባቢያ ስምምነትን ከከብዙአየሁ ታደለ እና ቤተሰቦቹ ፋውንዴሽን ጋር ተፈራርሟል።
ሁለቱ ተቋማት በተለይ ከሲሚንቶ ፋብሪካ ጋር ተያይዞ የሚሰተዋለውን የባለሙያ እጥረት መቅረፍ የሚያስችል የስልጠና ማዕከል በማቋቋም እንደሚሰሩም ተጠቁሟል። ስምምነቱን አስመልክቶ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ‘’ስምምነቱ ዩኒቨርሲቲያችን የመንግስት እና ግል ተቋማት አጋርነት (public private partnership) ስራዎችን በማስጀመር ቀዳሚ እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ እንደሀገር በሲሚንቶ ፋብሪካዎች አካባቢ የሚስተዋለውን የባለሙያዎች እጥረት የመቅረፍ እንዲሁም ከውጭ የሚመጡ ባለሙያዎችን በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የመተካት ዓላማን ያነገበ ነው’’ ብለዋል።
ዶ/ር ኡባህ አደም ስምምነቱ እውን እንዲሆን ትልቅ ሚና ለነበራቸው የፋውንዴሽኑ መስራች እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል ለሆኑት አቶ ብዙአየሁ ታደለ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ በስምምነቱን መሰረት ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
Share This News