Logo
News Photo

2ኛው ዙር የሀካቶን የፍጻሜ ውድድር ተካሄደ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልጸጊያ ማዕከል Iceaddis ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች ያዘጋጀው በOnline Learning and Skills Market Place ላይ ትኩረቱን ያደረገው 2ኛው ዙር የሀካቶን የፍጻሜ ውድድር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል ተካሄደ። 

በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከ35 በላይ የሚሆኑ ቡድኖች ያመለከቱ ሲሆን በወጣው የውድድር መስፈርት መሰረት ለመጨረሻው ዙር ያለፉት 13 ቡድኖች የሰሯቸውን ስራዎች በዛሬው እለት ለዳኞችና ጥሪ ለተደረገላቸው እንግዶች አቅርበዋል። 

በውድድሩ ላይ1ኛ ለወጣው Team Meba ቡድን 30,000.00 ብር፣ 2ኛ ለወጣው Team  መልህቅ ቡድን 20,000.00 ብር  እንዲሁም 3ኛ ለወጣው Team Nebula Tech ቡድን የ10,000.00 ብር ሽልማት ከእለቱ የክብር እንግዳና የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ከሆኑት ዶ/ር ተማም አወል ተበርክቶላቸዋል።

Share This News

Comment