Logo
News Photo

የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ተሰጠ

የሰው ሰራሽ አስተውሎት አገልግሎቶችን በአግባቡ መጠቀም የሚያስችል ክህሎትን ማዳበር የሚያስችል ስልጠና ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ተሰጥቷል። ስልጠናው በተለይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ይዟቸው የመጡትን አገልግሎቶች እና መተግበሪያዎች መለየት፣ የመተግበሪዎቹን አጠቃቀም ማስተዋወቅ እና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ተያይዞ ያሉ መሰረታዊ መረጃዎችን መስጠት ላይ ያተኮረ ነው።

በስልጠናው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም እንደተናገሩት የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በአግባቡ መጠቀም ዘርፈ ብዙ ተቋማዊ ፋይዳዎች እንደሚኖረው በመጠቆም ከሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በተቋም ደረጃ መመሪያ ተዘጋጅቶ በስራ ላይ እንደሚውል ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀውን ስልጠና በዘርፉ የትምህርት ዝግጅት እና የምርምር ልምድ ባላቸው / ተስፉ ጌትዬ አማካኝነት ተሰጥቷል። የካውንስል አባላቱ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ የሚነሱ ውስንነቶች እና ስጋቶችን ያነሱ ሲሆን ቴክኖሎጂውን በተመለከተ የሚስተዋለውን የመረጃ ክፍተት መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በማዘጋጀት መቅረፍ እንደሚገባ ተጠቁሟል።

 

Share This News

Comment