Logo
News Photo

አለም ለደረሰችበት የቴክኖሎጂ ፈጠራ የሜካኒካል ምህንድስና ሚና የጎላ መሆኑ ተነገረ። የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ቴክኖሎጂ ነክ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሜካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ምህንድስና ኮሌጅ በሜካኒካል ምህንድስና ዙሪያ የሚስተዋሉ የተዛቡ አመለካከቶችን ለማጥራት እና በዘርፉ ዓለም የደረሰበትን የቴክኖሎጂ አብዮት ለማመላከት ያለመ መድረክ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካሂዷል።

በዚሁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ / የሽሩን አለማየሁ እንደተናገሩት ‘’አለማችን ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልኩ በፈጣን የቴክኖሎጂ አብዮት ውስጥ ትገኛለች ያሉ ሲሆን የሰው ልጅን ኑሮ የሚያቀሉ አኗኗርን የሚያዘምኑ እጅግ ውስብስብ ቴክኖሎጂዎች ይፋ መሆን ጀምረዋል’’ ብለዋል። ከነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጀርባ የሜካኒካል መህንድስና እውቀት እና ሙያ ከፍተኛ አበርክቶ የነበረው መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዲዔታው ገልጸው ዘርፉ የሚፈልገውን እጅግ ብዙ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማዘጋጀት እንዲሁም በሜካኒካል ምህንድስና ዙሪያ የሚስተዋሉ የተዛቡ አመለካከቶችን ማጥራት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።

የሜካኒካል ምህንድስና ብረት መቁረጥ እና መበየድ ብቻ ማለት እንዳልሆነ የጠቆሙት ሚኒስትር ዲዔታው ይልቁንም ዘርፉ ከሞላ ጎደል ለሁሉም የምህንድስና ትምህርቶች መሰረት (Foundation) መሆኑን ገልፀዋል።

ምህንድስና የሰው ልጅን መሠረታዊ ፍላጎት ለማሟላትና የአኗኗር ስርዓት ለማሻሻል እንዲሁም ዘላቂ የልማት እድሎችን ለመፍጠር የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉት ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደም ናቸው። / ኡባህ አክለውም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ጥናት እና ምርምር በማከናወን፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በመፍጠር እና የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሙያ ማህበራቶች ላይ ተሳታፊ በመሆን ሀገራዊ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ /ፕሬዝዳንት / አብረሃም ደበበ እና የኢትዮጲያ ሜካኒካል ኢንጅነሮች ማህበር ምክትል ሰብሳቢ ሄኖክ ደረጀ ተገኝተው ጥናታዊ ፅሁፍ እና ቁልፍ ንግግሮችን አድርገዋል።

Share This News

Comment