Logo
News Photo

የኢንደስትሪያል ምህንድስና የቀድሞ ምሩቃን (አልሙናይ) ፓናል ውይይት ተካሄደ

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በመካኒካልና ኢንደስትሪያል ምህንድስና ኮሌጅ በኢንደስትሪያል ምህንድስና / ክፍል አዘጋጅነት የቀድሞ ምሩቃን (አልሙናይ) ፓናል ውይይት ተካሄደ።

በመድረኩ ታዳሚዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ ኤሊያስ አለማየሁ ጥሪውን አክብረው የተገኙ የቀድሞ ምሩቃንና መላ ታዳሚዎችን አመስግነው ፓናሉ የት/ ክፍሉን አበርክቶ ለመዘከርና በቀጣይ የቀድሞ ምሩቃንን እና ትምህርት ክፍሉን ለማቀራረብ እንዲሁም በወሳኝ ተቋማዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ገደፋየ በበኩላቸው ‘’ዩኒቨርስቲያችን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የሚያደርገው ሽግግር የበርካታ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ ይህን መሰል መድረኮች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው’’ ያሉ ሲሆን መድረኩን ላዘጋጀው / ክፍልና ኮሌጅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በማስከተልም ዩኒቨርስቲው እንደ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ምሩቃን አልሙናይ ህብረት ለመመስረት ሂደት ላይ መሆኑን አውስተው ይህ መድረክ እንደ ግብአት የምንጠቀምበትና በሽግግር ሂደት ባለድርሻ አካላትን የምናስተባብርበት አንዱ ስራ ነው ብለዋል።

በመድረኩ በአዲስ አበባ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አሲስታንት ፕሮፌሰር የሆኑት / አመኃ ሙሉጌታ ቁልፍ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የት/ ክፍሉን ቀጠናዊና ሃገራዊ ጉልህ ድርሻ፡ በዘርፉ የተሄደበትን የሰው ሃይል ልማትና ተግዳሮቶችን፡ ወቅታዊና መጻኢ እድሎችንና ሃላፊነቶችን ጨምሮ በርካታ ነጥቦችን ለታዳሚው አብራርተዋል።

በፓናሉ ከኢትዮጵያ ካይዘን የልህቀት ማእከል፡ ከዋቢ ግሩፕ፡ በግል ስኬታማ ስራ ከሚሰሩ እና ከሌሎችም ተቋማት የተጋበዙ የት/ ክፍሉ የቀድሞ ምሩቃን የተሳተፉበት ደማቅ የፓናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ተሳታፊዎች ተማሪዎችና መመህራን ውይይቶች ተካሂዷል።

Share This News

Comment