በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ህትመት፣ ስነ-ምግባር እና ስርፀት ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው ሴሚናር ሦስት የዩኒቨርሲቲው ሴት መምህራንና ተመራማሪዎች ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡበት ነው፡፡
በሴሚናሩ መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፋት የዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተርና የፕሬዝዳንት ተወካይ አቶ ቴዎድሮስ ገደፋዬ ዩኒቨርሲቲው በሁለንተናዊ መልኩ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሠራ ነው፡፡
ሴቶች በዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በመማር ማስተማር ፣ በጥናትና ምርምር ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ሆኖ ቆይቷል፡፡
ይሄንኑ ዝቅተኛ የሆነ ተሳትፎ ግምት ውስጥ በማስገባት በተሠሩ ስራዎች ላይ ባሳለፍነው በጀት ዓመት ሴቶች በዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ እንቅስቃሴ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ 20 በመቶ ማድረስ ተችሏል፡፡
በያዝነው የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመትም ሴቶች በዩኒቨርሲቲው ያላቸውን የ20 በመቶ ተሳትፎ ድርሻ ወደ 35 በመቶ ለማሳደግ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ አብራርተዋል፡፡
በተመሳሳይ ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት የተሠሩ ሥራዎችም አበረታች የሆነ ውጤት እያመጡ መሆናቸውንም ሳይንትፊክ ዳይሬክተሩ አቶ ቴዎድሮስ ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ለግማሽ ቀን በቆየው ሴሚናር ላይ ዶ/ር ነፃነት ተከስተ (
Climate change and women analyzing intersection, impact and context ) ፣በመምህርት ቤተል አሳልፈው (The Art of Items Writing; Addressing the burden and
Enhancing MCQ Quality ) እና በመምህርት ወይንእሸት ተስፋዬ ( Exploring the Agronomic and Environmental potential of
Bio Chars; Challenges and Futures Prospects) በሚል ርዕስ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
Share This News