Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 3 (ሶስት) ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችን የያዘ ልዑካን ብድን በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል በመገኘት በክልሎቹ በደረሰው ደርቅ ሳቢያ ለከፋ ጉዳት ለተጋለጡ ወገኖች የሚውል ለእያንዳንዱ የ1.5 ሚልዮን ብር (አንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሺ ብር) የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ 

ድጋፉን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እና ከፍተኛ አመራሩ በተገኙበት ለሱማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ለክቡር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ እና የኦሮሚያ ክልል የአደጋ እና መሪ ስጋት ኮሚሽነር አስረክበዋል። 

በመጨረሻም በድርቁ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከገንዘብ ድጋፉ በተጨማሪም በሌሎች መስኮች በቀጣይ ደግፉን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ዩኒቨርሲተው አረጋግጠዋል፡፡

Share This News

Comment