Logo
News Photo

‘’ትውልድ በመምህር ይቀረጻል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል’’ በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል። ‘’ትውልድ በመምህር ይቀረጻል ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል’’ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ውይይት ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሀላፊ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በምክትል ከንቲባ መዕረግ የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ /ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲሁም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እና መምህራን በተገኙበት ተካሂዷል።

የእለቱ የክብር እንግዳ እና የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ የውይይቱን አስፈላጊነት እና በውይይቱ ላይ የመምህራን የነቃ ተሳትፎ የሚኖረውን ፋይዳ አብራርተዋል። ምክትል ከንቲባው አክለውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሁለንተናዊ እድገት እና ብልፅግና እንዲረጋገጥ የማይተካ ሚና አላቸው ያሉ ሲሆን በተለይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ አስተዳደሩን በመደገፍ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ /ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት / መገርሳ ቃሲም መንግስት ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ለውጦችን እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው በተለይ በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን ሰርቷል ሲሉ ተናግረዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር /ፕሬዝዳንት / ተማም አወል ለውይይት መነሻ የሚሆን ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በተለይ ከሀገራዊ ለውጡ ጋር ተያይዞ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በተለይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ሚና ምን መምሰል እንደሚገባው የሚያብራራ ሰፊ ገለጻ አድረገዋል።

የቀረበውን ሰነድ መነሻ በማድረግ የዩኒቨርሲቲው መምህራን የተለያዩ ሀሳቦችን እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡት ጥያቄዎች እና አስተያየቶች የአስተዳደርሩ የመንግስ ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ /ቤት ሀላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ክቡር አቶ ኢብራሂም በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት ‘’መምህራን የተማረ የሰው ሃይልን በማምረት፣ ችግር ፈቺ እና አቅጣጫ ተቋሚ ምርምሮችን በመከወን ሀገራዊ ተልዕኳቸውን እየተወጡ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

Share This News

Comment