Logo
News Photo

የDigital course content አዘገጃጀትና Blended Learning አተገባበር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይርት እና የእውቅና መርሃ ግብር ተካሄደ

ውይይቱን እና የእውቅና መድረኩን በንግግር የክፈቱት የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደታናገሩት የኒቨርስቲያችን የመማር ማስተማርን ወደ blended learning እና online learning ለማዘመን የሚያስችሉ የተለያዩ ጉልህ ስራዎች መሰራታቸውን የገለጹ ሲሆን ከነዚህም መካከል 822 መምህራን የmasterclass ስልጠና እና 7180 መደበኛ ተማሪዎች ሰባት Student success suit ስልጠናዎች ወስደው በማጠናቀቅ ለe-learning ትግበራ ብቁ የሆኑ ሲሆን በተጨማሪም የመልቲሚዲያ እስቲዲዮ ተሰርቶ ስራ መጀመሩን ገልፀዋል፡፡ 

ዩኒቨርስትያችን በ2017 የትምህርት ዘመን ከፈረማቸው KPI መካከል 11 የሚደርሱ ፕሮግራሞችን/ኮርሶችን በblended መልኩ መስጠት መሆኑን አስታውሰው በዚህም እቅድ መሰረት 14 ፕሮግራሞችን/ኮርሶችን በ blended መልኩ መሰጠታቸውን ጠቅሰው ይህንን ለማሳካት ሲሳተፉ ለነበሩ መምህራን እና የsupervision አባላት አድናቆታቸውን ገልፀዋል፡፡ በቀጣይ አመትም ከዚህ ላቅ ያሉ ፕሮግራሞችን/ኮርሶችን በblended እንዲሰጡ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንሚያደርጉ በመግልፅ ውይይቱ ከፍተዋል፡፡

Share This News

Comment