ዩኒቨርሲቲው ነፃ ህግ አገልግቱን ተግባራዊ ማድረግ የሚጀምረው ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እና ከኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ማኅበር ጋር በመተባበር ነው፡፡
በፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ነፃ የህግ አገልግሎት ድጋፍን መስጥ የጀመረው ገና ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ኡባህ አክለውም "ነፃ የህግ አገልግሎት ድጋፉ በተለያዩ ምክንያቶች ለተወሰኑ ዓመታት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም ዘንድሮ እንደ አዲስ በመጀመር ተጋላጭና አቅመ ደካማ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል’’ ያሉ ሲሆን ‘’የዛሬው ፕሮጀክትም ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ነፃ የህግ ድጋፍ አገልግሎት ከማጠናከር እና ማህበረሰብ ተኮር ተልዕኮዎቹን እንዲያሳካ አቅም ይሆናል’’ ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው የያዘውን ግብ እንዲመታ የሁሉም ወገን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን ያስገነዘቡት ፕሬዝዳንቷ ለፕሮጀክቱ ስኬትም ሁላችንም የበኩላችን ለመወጣት እንዘጋጅ በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
በመክፈቻ ፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ህግ ትምህርት ቤቶች ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ደርሶልኝ የእኔአባት በበኩላቸው ማኅበራቸው ከተቋቋመበት ካለፋት 3 ዓመታት ወዲህ በ3 ዋና ዋና የትኩረት መስኮች እና በ42 ዩኒቨርሲቲዎች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡
Share This News