Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል በክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሀገር አቀፍ ሽልማትን አግኝቷል

በ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት በጎ ፍቃድ ስራዎች ላይ ሰፊ ማህበራዊ ተሳትፎ ያደረገው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ከጤና ሚኒስቴር እውቅና አግኝቷል።  ሆስፒታሉ ከ34ሺ በላይ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተደራሽ ያደረገ የጤና ምርመራ፣ ህክምና እና ማማከር ስራዎችን የሰራ ሲሆን በቋሚነትም ታካሚዎችን በሆስፒታሉ ተቀብሎ በከፊል የጤና አገልግሎት እየሰጠ ስለመሆኑ ተጠቁሟል። 

ሽልማቱን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰፊ ማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ከጤና ሚኒስተር የተገኘው ሽልማትም ለዩኒቨርሲቲው ጥረት የተሰጠ እውቅና መሆኑን ተናግረዋል። ለሽልማቱ መገኘት ታላቅ አበርክቶን ላደረጉት የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት፣ የሆስፒታሉ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች እንዲሁ መላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ያመሰገኑት ዶ/ር ሁሴን የ2017 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሀገር አቀፍ ደረጃ በይፋ መጀመሩን በመግለፅ ለመላው የሆስፕታሉ እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሰራተኞች የተለመደ ሀገራዊ አደራቸውን ለመወጣት እንዲዘጋጁ ጥሪ አስተላልፈዋል።

Share This News

Comment