በመትከል ማንሰራራት’ በሚል መሪ ቃል የሚደረገው የ2017 ዓ/ም ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ዪኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል በድምቀት ተጀምሯል። በመርሃ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ፣ የክልል መስተዳድር አመራሮች፣ ሚኒስትሮች፣ ሚንስትር ዲኤታዎች፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ አባላቶች እና የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተገንተው ችግኝ ተክለዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዝዳንት እና የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አደም ፋራህ በአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገንተው እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአካባቢን ገፅታ ከመቀየር፣ የምግብ ማስትናን ከማረጋገጥ፣ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን ከማገዝ እና የስራ እድልን ከመፍጠር አኳያ ሰፊ አበርክቶ ያለው መሆኑን ጠቁመዋል። ችግኞች እንደ አካባቢው መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ እና የአየር ፀባይን መሰረት ባደረገ መልኩ እንደሚተከሉ የተናገሩት ም/ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ ከዚህ አኳያ የድሬዳዋ አስተዳደር ችግኞችን ከመትከል፣ ከመንከባከብ እንዲሁም አቅም በፈቀደ መጠን ለጎረቤት ሀገራት ጭምር ድጋፍ በማድረግ ላበረከተው ጉልህ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃርቢ ቡህ በበኩላቸው ‘’በ2017 ዓ/ም ብቻ ኢትዮጲያ 7.5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ እየሰራች መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ኢትዮጲያ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአለም ሃገራት ተመኩሮ የሚሆን ሰፊ የአየር እና አካባቢ ጥበቃ ስራዎችን እየሰራች ነው ብለዋል።
Share This News