Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች በእቅድ ዝግጅት ፣ ክትትል እና ግምገማ እስመልክቶ ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በስልጠናው መድረክ ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ሁሉም አመራሮች የዪኒቨርስቲውን እስትራቴጂክ ዕቅድ፣ ራዕይ እና ተልዕኮ ከማሳካት ረገድ በዕቅድና ክትትል ዙሪያ ያለው ክፍተት ለመፍታት በስልጠናው ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸዋል። 

የዩኒቨርሲቲው ሁሉም አመራሮች የሚሳተፉበት እና በእቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ ላይ ያላቸውን አቅም ለመገንባት ታሳቢ ያደረገው ስልጠና ለተከታታይ ሦስት ቀን የሚቆይ ሲሆን ከኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት በመጡ ከፍተኛ ባለሞያዎች የሚሰጥ መሆኑን የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የእቅድ፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፋሚ አባስ አስታውቀዋል፡፡

ስልጠናው ለቀጣይ ሦስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በየደራጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑበት ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡  


Share This News

Comment