በብልፅግና ፓርቲ የ2017 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች ማጠቃለያ የግምገማ መድረክ ላይ የተገኙ ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እና የፓርቲ አመራሮች የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታልን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሆስፒታሉን የማጠናቀቂያ ስራ በመስራት እና ለህክምና አገልጎሎት የሚያስፈልጉ ግባዓቶችን በማሟላት ከፊል አገልግሎት መጀመሩን እና በአንድ አመት ውስጥ ብቻ ከ 10 ሺህ በላይ የአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት መስቱን የሆስፒታሉ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ ለእንግዶች አብራርተዋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሆስፒታሉ የሚያስፈልጉ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን፣ እጅግ ዘመናዊ የታካሚ መኝታ አልጋ፣ የድገተኛ ክፍል እና ፋርማሲ በማደራጀት ሆስፒታሉ በከፊል አገልግሎት እንዲሰጥ ማስቻሉም በጉብኝቱ ወቅት ተመላክቷል።
በጉብኝቱን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የብልፅግ ና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፓርቲው ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህ እንደተናገሩት የመማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ከአካባቢው ማህበረሰብ አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም ጭምር አገልግሎት መስጠት የሚችል፣ የህክምና ቱሪዝምን የሚያጎለብት እንዲሁም ቀጠናዊ ት ስ ስርን የሚያጠነክር ሃብት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
Share This News