የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ማህበራዊ ትስስራችን ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ቃል የጎንደር የቃል ኪዳን ቤተሰብ ትስስርና ትውውቅ ሀገር አቀፍ የልምድ ልውውጥ አካሂዷል፡፡
በዚህ መርሀ-ግብር የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ ተማሪዎችን ‘’የቃል ኪዳን ቤተሰብ’’ በማድረግ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ እና የጎንደር ከተማ ነዋሪ ጋር ቤተሰብ የሚሆኑበትን እድል በማመቻቸት ሰፊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። ይህንኑ ተመኩሮ በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተግባራዊ እንዲሆን የሚያስችል ስምምነት በማስፈለጉ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከተማ መስተዳደሮች እንዲሁም የሰላም ሚኒስተር ስምምነት አድርገዋል። ስምምነቱ የ ፋሲለደስ ስምምነት (Fasiledes Declaration) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲም የስምምነቱ አካል መሆን ችሏል።
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በኩል ስምምነቱን የፈፀሙት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንደተናገሩት ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መልካም ተሞክሮዎችን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች በመቀመር የሚሰራ መሆኑ ገልፀው ተማሪን ከማህበረሰቡ ጋር ማቀራረብ እንዲሁም ቤተሰባዊ ትስስር መፍጠር ለተማሪውም ሆነ ዩኒቨርሲቲው ለሚገኝበት አካባቢ ማህበረሰብ በርካት ጠቀሜታ ይኖረዋል በለዋል።
Share This News