Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በሀገር በቀል ዕውቀቶች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ያሉ የሀገር በቀል ዕውቀቶችን ዙሪያ በትብብር ምርምር ለመስራት፣ ካሪኩለም ለመቅረጽ፣ አወደ ጥናቶችን በትብብር ለማዘጋጀት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በስምምነት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል እንደተናገሩት ‘’ ሀገር በቀል እውቀት የአንድ አካባቢ ማህበረሰብ ከአካባቢያዊ ሁኔታ ጋር ባለው ቁርኝት የሚገኝ እና የሚዳብር እንዲሁም ራሱን ከተፈጥሮ ጋር አስማምቶ ለማኖር የሚያስችል በዘመናት ሂደት የተገኘ እውቀት  መሆኑን በመግልጽ ምስራቁ የሀገራችን ክፍል በሀገር በቀል ዕውቀቶች የበለፀገ እና ለሀገር ዘርፈ ብዙ አብርክቶት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል። ዶ/ር ተማም አክለውም ሁለቱ ዩኒቨርስቲዎች በሀገር በቀል እውቀቶች ላይ የሚያደርጉት ትብብር የማህበረሰቡ ውድ እቅቀቶች እና ክህሎት ተጠብቆ እንዲቆይ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። 

በተጨማሪም፣ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ም/ል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይስሐቅ የሱፍ ‘’ዛሬ የተፈራረምነው የመግባቢያ ሰነድ በምስራቁ የሀገራችን ክፍል ብሎም እንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ለማከናወን የሚረዳና አባቶች ያቆዩልንን እነኝህን እውቀቶች ለአካባቢውና ለሀገር በሚጠቅም መንገድ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በዲጂታል መንገድ በመስነድና ምርምር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርገን መስራት የሚያስችል’’ ነው ብለዋል።

Share This News

Comment