Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በክረምት የበጎ ፍቃድ መርሃ ግብሮች 50 ሺህ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራ ተጠቆመ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራን በይፋ አስጀምሯል። ዩኒቨርቨርሲቲው በተለይ በጤናው ዘርፍ በሰጣቸው የክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች በሀገር ደረጃ ለተከታታይ ሁለት አመታት ተሸላሚ የሆነ ሲሆን ይህንኑ የበጎ ስራ ዘንድሮም በተጠናከረ መልኩ ለመስጠት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ‘’ዩኒቨርሲቲው የ Covid ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀመሮ በጤናው ዘርፍ ሰፊ የማህበረሰብ አገልግሎትን ሲሰጥ ቆይቷል’’ ብለዋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ በሚደረገው የክረምት በጎ ፍቃድ ንቅናቄ አካል በመሆን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የበጎ ፈቃድ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል 

የዩኒቨርሲቲው ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል በበኩላቸው በዝንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ በጤናው ዘርፍ ከሚደረገው ድጋፍ በተጨማሪ አቅመ ደካሞችን ማዕከል ያደረገ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ (ለ 1000 ተማሪዎች) ፣ የቤት እድሳት፣ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የትምህርት ቤት እድሳት እና የመማሪያ ግብዓት የማሟላት ስራዎችን እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይረክተር ዶ/ር ሆሴን መሀመድ በበኩላቸው ‘’የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና አካዳሚክ ስታፍ አባላት በተለይ በ2016 ዓ/ም በተሰራው የበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ ባሳዩት ትጋት በሀር ደረጃ በመሸለማቸው የእንኳን ደስ አላችሁ

Share This News

Comment