Logo
News Photo

በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በድምቀት ተከናውንዋል ።

የ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ‘በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል 7.5 ቢሊየን ችግኞችን በሀገር ደረጃ ለመትከል ታስቦ እየተሰራ ይገኛል። የዚሁ ንቅናቄ አካል የሆነው እና በአንድ ጀንበር (12 ሰዓት ውስጥ) 700 ሚሊየን ችግኞችን ለምትከል ታስቦ የተዘጋጀ መርሃ ግብር ዛሬ በመላው የሀገራችን ክፍል ተካሂዷል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች እና ተማሪዎችም ይህንኑ ሀገራዊ ንቅናቄ በመቀላቀል ዛሬ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኞችን ተክለዋል። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት እንደተናገሩት ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ/ም የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ቀደም ብሎ መጀመሩን ጠቅሰው በተለይ በዩኒቨርሲቲ መማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ሰፊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ማከናወኑን አስታውሰዋል። ዶ/ር ኡባህ አያይዘውም ‘’ዩኒቨርሲቲው የዛሬውን ጨምሮ በርከት ያሉ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሮችን ያዘጋጀ መሆኑን በመጥቀስ በዛሬው መርሃ ግብር ላይ ተሳትፎ ላደረጉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል። 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በሀገር ደረጃ እያስገኘ ስለሚገኘው እምርታ እና ሳይንሳዊ ኩነቶች ዙሪያ የተመራማሪዎችን ሀሳብ ይዞ ይዞ የሚቀርብ ይሆናል።

Share This News

Comment