Logo
News Photo

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እና አመራሮች ልዩ አቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጠ ነው

በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ  ካለፈው ሀምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከድሬደዋ አስተዳደር እና ከሶማሌ ክልል የተወጣጡ 336 የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች ልዩ የክረምት  የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

በዩኒቨርስቲው የመምህራን ልማትና ተከታታይ የሙያ ማሻሸያ ኦፊሰር የሆኑት መምህር ምንተስኖት ቦጋለ ስልጠናውን አስመልክቶ እንደተናገሩት በአገራችን ለትምህርት ጥራት መጓደል ከሚነሱት ምክንያት መካከል የመምህራን እና የትምህርት አመራሩ ብቃት ከሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመገኘቱ ስልጠናውን መስጠት አስፈልጓል ብለዋል፡፡

የዚህ ልዩ የክረምት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ዋነኛ አላማ የመምህራን እና የትምህርት አመራሩን የሙያ ብቃትና ተወዳዳሪነት በማሰደግ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል በማድረግ ሀገርን እና ወገንን የሚጠቅሙ ዜጎችን ማፍራት መሆኑን የሚያ ማሻሻያ ሶፊሰሩ ተናግረዋ፡፡

ስልጠናው የተለያዩ የትምህርት አይነቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰጥ ሲሆን ለማህበራዊ ሳይንስ መምህራን ለከታታይ 20 ቀን እንዲሁም ለተፈጥ ሳይንስ መምህራን ለተከታታይ 26 ቀን የሚሰጥ መሆኑ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችልዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰልጣኞች በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊው የትምህርት ቁሳቁስ፣ የማደሪያ ቦታ፣ ምግብ አገልግሎት እና የቤተ ሙከራ ግብዓቶችን በማሟላት ሰልጣኞችን እያስተናገደ መሆኑ ተጠቁሟል።

Share This News

Comment