Logo
News Photo

ለድሬደዋ ዩኒቨርስቲ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች የትምህርት አመራርነትን ክህሎት (Academic Leadership) አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለትምህርት ክፍል ኃላፊዎችና አስተባበሪዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዋነኝነት በትምህርት አመራርነት ክህሎትን ማዳበር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠተና ሲሆን በዚሁ ስልጠና መክፈቻለ ላይም የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንዳሉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገውን ሽግግር ስኬታማ ለማድረግ ከትምህርት ክፍል አመራሮች ብዙ ይጠበቃል ብለዋል፡፡ 

ይህንን ታሳቢ በማድረግም ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም የትምህርት አመራሩን አቅም ማሳዳግ የሚችሉ የተለያዩ ተከታታይነት ያላቸው ስልጠናዎችን ያዘጋጃል ያሉት ዶ/ር መገርሳ ሰልጣኞቹም ስልጠናውን በአግባቡና በንቃት በመከታተል የሚጠበቅባቸውን ይወጡ ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በተለይም ድሬዳዋ የምስራቁ የሃገራችን ክፍል የኢንደስትሪ ማዕከል የመሆን ርዕይዋን ማሳካት እንድትችል ዩኒቨርሲቲው የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በመሆን የበኩሉን መወጣት እንዲችል እና በሃገራችን ተመራጭ፣ በአፍሪካ ደግሞ ተወዳዳሪ ለመሆን የያዘውን ርዕይ ለማሳካትም የትምህርት ክፍል አመራሩ የሚጫወተው ሚና  ጉልህ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተገልፆል፡፡

ለተከታታይ ሁለት ቀናት የቆየውና የትምህርት አመራርነትን ክህሎት (Academic Leadership) ላይ ትኩረት ያደረገውን ስልጠና ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በመጡ የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ከፍተኛ ባለሞያዎች የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በፋይናንስና ግዥ ክፍሎች አካባቢ ጎልተው የሚታዪትን ችግሮች በዘላቂነት መቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ለመካካለኛ አመራሩ እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀግብር ላይ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment