በጤና ሚኒስቴር የጤና ስርዓት እና አቅም ግንባታ ሚኒስቴር ዴኤታ ሰሀረላ አብዱላህ እና የሚኒስቴሩ የሀብት አስተዳደር እና የቁጥጥር ሚኒስትር ዴኤታ ፍሬሂወት አበበ የተመራ ላኡክ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታልን ጎበኘ።
የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ዛሬ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል። የስራ ሃላፊዎቹ በዋናነት ሆስፒታሉ እየሰጠ ያለውን የጤና አግልግሎቶች እና መሰረተ ልማት ተዟዙረው የጎበኙ ሲሆን ሆስፒታሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ የማህበረሰቡን ክፍል ተደራሽ የሚያደርግ ስራ መስራት መቻሉ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ እና ሪፈራል ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ ሆስፒታሉ ያለበትን ደረጃ እና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ‘’ሆስፒታሉ የሜዲካል ቱሪዝም ማእከል ለመሆን የረጅም ጊዜ ርዕይ ሰንቆ እየሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ሚኒስትር ዲኤታዎቹ ሆስፒታሉ በየክረምት የበጎ ፈቃድ ጤና አገልግሎት ስራዎችን በመመልከት እና የጤና ምርመራ በማድረግ ተሳትፎ አድርገዋል።
Share This News