Logo
News Photo

አርሶ እና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርግ እና በስድስት የምስራቅ ኢትዮጲያ ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የሚሰራ ፕሮጀክት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆነ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ እና ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲዎች በትብብር የሚሰሩት እና የአየር ንብረትን የሚቋቋም የተቀናጀ የግብርና ስራ እንዲሁም የአርሶ እና አርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ዛሬ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ይፋ ሆኗል። 

ፕሮጀክቱ በዋናነት ደረቃማ እና የአፈር መሸርሸር ችግር ያለባቸውን አካባቢዎች መለየት፣  የተጎዱ የመሬት ክፍሎችን እንዲያገግሙ ማስቻል፣ ውሃን የማቆር ፣ ቆሻሻ እና ተረፈ ምርቶችን በመጠቀም የተፈጥሮ ማዳበሪያን የማምረት፣ የተቀናጀ የአሳ፣ ዶሮ እና ፍራፍሬ ምርትን ለማህበረሰቡ ማስተዋወቅ፣  የሽፈራው ተክልን (ሞሪንጋ) ለአርሶ እና አርብቶ አደሩ ማህበረሰብ ማስተዋወቅ እንዲሁም ተጠቃሚ የማድረግ ሰፊ ስራዎችን ያካታተ እንደሆነ ታውቋል።

በፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ‘’ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙበት ማህበረሰብ የላቀ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል’’ ያሉ ሲሆን በትብብር የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ውስን ሀብትን በአግባቡ ከመጠቀም፣ በርካታ የማህበረሰቡን ክፍል ተደራሽ ከማድረግ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎላ ስራዎን ለመስራት የሚያስችል በመሆኑ መሰል የትብብር ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

Share This News

Comment